የወላጅ/አሳዳጊ እና ተማሪ ውሎችን መቀበል
የካምብሪጅ ማህበረሰብ ቻርተር ትምህርት ቤት የተማሪ እና ቤተሰብ መመሪያ የጅ መጽሀፍን ማግኘት እንድምችል እና ፖሊሲዎቹንም የምቀበላቸው መሆኔን አረጋግጣለሁ። ይህንን መመሪያ መጽሀፍ ሙሉ በሙሉ ማንበብ እና ስለልጄ ትምህርታዊ ስኬት እና ስለባህሪው/ዋ ሁኔታ ከCCSC ምን ተስፋ እንደሚጠበቅ ከልጄ ጋር የመወያየት ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘባለሁ።
በልጄ የትምህርት ሁኔታ ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለብኝ እና ከአስተማሪዎች እና ከ CCSC የስተዳደር ሰራተኞች ጋር ግልጽ ተግባቦት ማድረግ እንደሚጠበቅብኝ እገነዘባለሁ።
በCCSC የተማሪ እና ቤተሰብ መመሪያ መጽሀፍ ውስጥ የጸረ-ማዋከብ እና ጸረ-ጉልበተኛነት ህጎችን የሚመለከተውን ክፍል ያነበብኩ መሆኔን እና፣ እነዚህ ህጎችም በካምብሪጅ ማህበረሰብ ቻርተር ትምህርት ቤት ውስጥ በጥብቅ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ የተረዳሁ መሆኔን አረጋግጣለሁ።
የቤተሰብ የትምህርታዊ መብቶች እና የግላዊነት ድንጋጌ (FERPA) የሚመለከተውን ክፍል እና ልጄ 18 ዓመት ወይም በላይ ሲሆን/ስትሆን፣ የልጄን የትምህርት ቤት ሬኮርዶች ለማግኘት፣ ለማሻሻል፣ እና ይግባኝ ለማለት የሚያስችሉ የአሰራር ሂደቶችን በሚመለከት በCCSC የተማሪ እና ቤተሰብ መመሪያ መጽሀፍ ውስጥ ያነበብኩ መሆኔን አረጋግጣለሁ።
የCCSCን የምክር እና የተማሪ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍልን ያነበኩ መሆኔን እና፣ ልጄ እነዚህን አገልግሎቶች ያለወላጅ ስምምነት እንዲያገኝ የማልፈልግ ከሆነ፣ በ rgalvin@ccscambridge.org ወይም (617) 354-0047 x241 በኩል ሮዝሜሪ ጋልቭን (Rosemarie Galvin)ን ተገናኝቼ ማነጋገር እንደምችል የተረዳሁ መሆኔን አረጋግጣለሁ።
የተማሪ እና ቤተሰብ መመሪያ መጽሀፉን በሚመለከት ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ከሉኝም፣ ከልጄ አማካሪ ወይም ከትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ቡድን አባል ጋር ለመገናኘት፣ ለትምህርት ቤቱ የስልክ ቁጥር (617) 354-0047 እደላለሁ፣ ወይም ለ info@ccscambridge.org ኢሜል አደርጋለሁ።