ስሜ ከላይ የተጠቀሰው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብያለሁ፡፡ ከዚህ በታች በተጠቀሰው በቤተክርስቲያኒቱ የእምነት አንቀጽና በመተዳደሪያ ደንቧ እስማማለሁ፡፡ --------------------------------------------------------------------------------------------------የቤተክርስቲያኒቱ የእምነት አንቀጽ -----/////////////////////////////////////////////////////////////////////////// አንቀጽ1. ፍጹምና ዘላለማዊ በሆነው ሁሉን በፈጠረው በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አምናለሁ (ዘፍ 1:1, መዝ 139:1-6,፣ 19:1 ኤር 23:23፣ ኢያ3:10, ራእ. 4:11)፡፡2. ክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው በመንፈስ ቅዱስ ተጸንሶ ከድንግል ማርያም እንደተወለደ፣መጻሕፍት እንደተነበዩት ለኃጢአታችን መስዋዕት በመሆን በመስቀል ላይ እንደሞተ፣ በሥጋ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ፣ እንዳረገና የእኛ ሊቀካኅንና ጠበቃ ሆኖ በመንግሥተ ሰማያት በአባቱ ዘንድ በታላቅ ክብር አንደሚገኝ አምናለሁ (ዮሐ3:13፡31, 10:30, 17:5፣ቆላ1:16፣ ዕብ1:2፣ ማቴ1:18፣ ሉቃ1:35,፣ዮሐ 4:6፣ ማቴ 21:8,፣ዮሐ1:35፣ ሮሜ5:12-21,፣ 1ቆሮ15:22፣ 2ቆሮ5 15-21,፣ማቴ 28:8-10, ሉቃ24:34፣ ዮሐ20:26-29, የሐዋ1:12)3. በእግዚአብሔርና በሰው መካከል አንድ አማላጅ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ አምናለሁ (ሮሜ 8:34, ዕብ 7:25 1ጢሞ 2:5)4. በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ደምና ትንሳኤ ምክንያት ሰው ደኅንነት እንደሚያገኝ ከፍርድም ነጻ እንደሚሆን ክርስቶስንም የተቀበሉት ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ በመወለድ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚሆኑ አምናለሁ (ሮሜ 5:9፣ 2Cor.5:15-21, ቲቶ 3:5)5. መንግስቱን ሊመሠርት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና እንደሚመለስ፣ በሙታን ትንሳኤና በዘላለም ፍርድ አምናለሁ፡፡ (ዮሐ 14:1-3፣ 1ቆሮ 15:51-57፣ 1ተሰ 4:13-18, ቲቶ2:11-14)6. በጥንት እንደነበረው በዘመናችንም መንፈስ ቅዱስ በሙሉ ኃይሉ በሰዎች ሕይወት ውስጥ እንደሚሠራ አምናለሁ (የሐ 14:16-17, 7:37-39 ሮሜ8:26, 2ቀሮ1:22 2ተሰ 2:13)7. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደሚያከብር፤ ሰዎችንም ስለኃጢያአት በመውቀስ፣ ሕይወትን በማደስ፣ በልብ ውስጥ አድሮ በመምራትና በማስተማር ለአገልግሎትና ለቅዱስና ኑሮ ኃይልና እንደሚ ሰጥ አምናለሁ (የሐዋ 1:8, 1ቆሮ 12:13፣ 1ቆሮ 6:19፣ አፌ1:13)፡፡8. ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሮ ሳለ በኃጢአት ምክንያት የጠፋ እንደሆነ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ደኅንነት እንደሚያገኝአምናለሁ(ዘፍ 1:26 ፣ 1ቆሮ11:7,፣ ያዕ3:9፣ ዘፍ 3:1-17፣ ሮሜ 1:21, 28፣ዮሐ.3:5-7, ቲቶ.3:5)፡፡9. የክርስቶስ እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው የሕይወት ለውጥ ያገኙ ሰዎች ኅብረት እንደሆነ ይህም ኅብረት የክርስቶስ አካል እንደሆነና የአካሉራስ ክርስቶስ እንደሆነ አምናለሁ(የሐዋ 7:29፣ 19:39, ኤፌ 1:22-23፣ ሮሜ6:5፣ 1ቆሮ 10:32፣ 1ጴጥ2:9)፡፡10. በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ጥምቀትንና የጌታ እራት ሥርዓቶች ሊካፈሉ እንደሚገባ አምናለሁ፡፡ (ማቴ28:19-20, የሐዋ8:38, 35-39፣ 9:18, 10:47, 16:14)፡፡11. ሙታን ሁሉ ከመቃብር በሥጋ እንደሚነሱና በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ወደ ዘላለም ደስታ፣ ያለመኑት ግን ወደዘላለም ቅጣት አንደሚሄዱ አምናለሁ (መዝ17:15፣ ዳን12:1-2፣ ማቴ22:29፣ ዮሐ.5:28-29, የሐዋ2:31,4:2, 33፣ 18:32, 1ቆሮ15:17፣ 1ተሰ4:16፣ 2Tim.2:18፣ራእ 20:4-5)፡፡12. መጽሐፍ ቅዱስ (ማለትም ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን)ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነቀፋ የሌለበት እግዚአብሔር የድነት ፈቃዱንና የመለኮቱን ኃይል የገለጸበት የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አምናለሁ (2ጢሞ 3:16, 2ጴጥ 1:21)13. ጋብቻ በቃሉ እንደተደነገገው በአንድ ወንድና ሴት መሀል የሚፈጸም እግዚአብሔር ያቋቋመው ሕይወት መሆኑን አምናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ግብረ ሥጋን የፈቀደው በጋብቻ በተሳሰሩ ወንድና ሴት መካካል ብቻ መሆኑን አምናለሁ ከዚህ ያፈነገጡ ሁሉ ኃጢአት ነው፡፡ በመሆኑም ዝሙት፣ ምንዝርና፣ ግብረሰዶማዊነት፣ ወንደቃነት፣ እንሰሳን መገናኘት፣ዘመድን ማስነወር፣ ሴሰኝነት ወይም ጾታን መለወጥ: የተፈጥሮን ጾታ አለመቀበል በጌታ ፊት የተጠላ መሆኑን አምናለሁ፡፡ (ዘፍ.1:28-29፣2:18-25, ማቴ19:1-9, ማር 10:2-9, ኤፌ 5:25) *