እንኳን ወደ ኒቆዲሞስ የ'Online' አብነት ትምህርት መማርያ በደኅና መጡ!
- ኒቆዲሞስ የማታ ትምህርት በየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ሁኔታ ላይ ለሚገኝ ሰው መሠረታዊ የአብነት እና የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ማዳረስ ዓላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊ ኦንላይን ትምህርት ቤት ነው።
1. ኒቆዲሞስ ይህን የአብነት ትምህርት የሚያስተምርበት ዋና ዋና ዓላማዎች ፦
1. ምእመናን በልሣነ ግዕዝ የቤተ ክርስቲያን ጸሎቶችን መጸለይ እንዲችሉ እና ዜማዋን ተምረው በሥርዓተ አምልኮዋ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ማድረግ።
2. ምእመናን በቅዱስ ያሬድ በኩል ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠውን የዜማ ጸጋ ዐውቀው እንዲመሰጡበት እና የቤተ ክርስቲያኒቱንም ውበት እንዲረዱ ማድረግ።
3. ዲያቆን ወይም ካህን ለመሆን የሚያበቁ ዕውቀቶች ተደራሽ ማድረግ።
4. በካህናት እጦት እና በቀዳሽ አለመኖር ምክንያት እየተፈጠሩ ላሉ ችግሮች፣ በብቃት የተማሩና የሠለጠኑ አዳዲስ ካህናትን በማውጣት የመፍትሔ አካል መሆን።
5. ዘመኑን በዋጀ መንገድ ነባሩን የቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ማስፋፋት እና ለሁሉም ምእመናን ተደራሽ ማድረግ።
2. የሚያስተምሩን መምህራን
- ትምህርቱን የሚያስተምሩን መምህራን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአብነት ትምህርት ቤት ያለፉ እና በዕውቀታቸው የተመሰከረላቸው ሲሆኑ፣ ከስድስት ዓመታትም በላይ የማስተማር ልምድ ያላቸውና በትምህርት አሰጣጥ ዘዴያቸውም የተመሰገኑ ናቸው።
3. የትምህርቱ አሰጣጥ
- ትምህርቱ 'Google meet'ን የመሰሉ አማራጮችን በመጠቀም የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- የትምህርት መማርያ ቀን እና ሰዓት መምህሩና ተማሪዎች ተወያይተው የሚወስኑት ይሆናል፡፡